ለስራ ዝግጁነት ምሽት ሰኞ፣ ዲሰምበር 14፣ 2015 7:00–9:00 p.m. Gaithersburg High School 101 Education Boulevard Gaithersburg, MD 20877 ከ7ኛ እስከ 10ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ያውቁ ይሆን ቢዝነሶች ሊያሟሏቸው የማይችሉ ከፍተኛ ክፊያ የሚከፈልባቸው ስራዎች እንዳሏቸው? እነዚህ ስራዎች ምን እንደሆኑና የMCPS የኮርስ መንገዶች እንዴት ተማሪዎችን ለነዚህ አስደናቂ ስራዎች እንዴት እንደሚያዘጋጁ ለማወቅ ሰኞ፣ ዲሰምበር 14፣ በGaithersburg High School ተቀላቀሉን። ስለ እድሎች ከመምህራን፣ ተማሪዎች እና ከቢዝነስስና ከከፍተኛ ትምህርት አዳምጡ በ— •ኪነጥበባት፣ ሂውማኒቲስ፣ ሚድያ እና መገናኛዎች •ባዮሳይንሶች፣ የጤና ሳይንስ፣ እና ህክምና •ቢዝነስ አስተዳደርና ፋይናንስ •ህንፃና ብልፅግና/Construction and Development •ትምህርት፣ ስልጠና እና የልጅ ጥናቶች •ኤንጂኒሪንግ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ እና የመፈርበክ ቴክኖሎጂዎች •አካባቢያዊ፣ የእርሻ፣ እና የተፈጥሮ ሀብቶች •የሰውና የበላተኛ/ተጠቃሚ አገልግሎቶች፣ እንግዳ አቀባበል፣ እና ቱሪዝም •የመረጃ ቴክኖሎጂ •ሕግ፣ መንግስት፣ የህዝብ ደህንነት፣ እና አስተዳደር •ትራንስፖርት፣ ስርጭት፣ እና ሎጂስቲክስ/ስንቅና አቅርቦቶች •የወጣት ተጠባባቂ መኮንኖች የስልጠና ክፍለ ሰራዊት ከወላጆቻቸው ጋር እንዲያዳምጡ ተማሪዎች ተጋብዘዋል። ነፃ የህፃናት እንክብካቤ (እድሜ 4 አመትና ከዚያ በላይ) እና የውጭ ቋንቋ ትርጉም ይቀርባሉ። 0616.16 • EGPS • Amharic • NP
© Copyright 2026 Paperzz