CCRCA Letter - Amharic

ኦክቶበር 12፣ 2015
የተከበራችሁ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች/አሳዳጊዎች፡አሁን የምፅፍላችሁ በ11ኛ ክፍል በሚገኙ ተማሪዎች ላይ በዚህ አመት ተግባራዊ የሚሆን በስቴት ስለተሰጠ አዲስ አደራ
መመርያ እና በMontgomery County Public Schools (MCPS) እንዴት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ነው።
የሜሪላንድ General Assembly/ፓርላማ፣ ሁሉንም የህዝባዊ ት/ቤት ተማሪዎች 11ኛ ክፍልን ሲጨርሱ በእንግሊዘኛና
በሂሳብ የኮሌጅና ለስራ ዝገጁነት ግምገማ እንዲወስዱ የሚያስገድደውን፣ የCollege and Career Readiness and
College Completion Act of 2013/የ2013 የኮሌጅና የስራ ዝግጁነት እና የኮሌጅ ማጠናቀቅ አዋጅ (CCRCCA)
አስተላለፈ። The Maryland State Department of Education/የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት መምርያ (MSDE)
ይህን ግዴታ እንዲያሟሉ ለአካባቢ ት/ቤቶች የተለያዩ አማራጮችን አቅርቧል። MCPS ይህን መምርያ በተማሪዎችና
በቤተሰቦቻቸው ላይ እጅግ አነስተኛ ተፅእኖ በሚያደርስ መንገድ ለመተግበር መርጧል።
MCPS SAT፣ ACT፣ እና ACCUPLACERን በCCRCCA ስር ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁነት ግምገማ
ይጠቀምባቸዋል። በአሁኑ ወቅት፣ ከተማሪዎቻችን ከ70 በመቶ በላይ SAT እና/ወይም ACT ይወስዳሉ፣ ሌሎች ደግሞ 11ኛ
ክፍል መጨረሻ ላይ ACCUPLACERን ይወስዳሉ። የልጅዎ ት/ቤት 11ኛ ክፍል መጨረሻቸው ላይ ተማሪዎች ከነዚህ
ቢያንስ አንዱን የመውሰድ አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ለተማሪዎችና ለቤተሰቦች ተጨማሪ መረጃዎች ይሰጣል።
ሕጉ የተጨማሪ ገንዘብ ጉዳይ ይዞ ስላልወጣ፣ ወላጆች ልጃቸው ACTን ወይም SATን እንዲ(ድት)ወስድ መክፈላቸውን
ይቀጥላሉ፣ ነገር ግን እነዚህን ፈተናዎች በሚያስተዳድሩት በኩል የፋይናንስ እርዳታ ይቀርባል። ACCUPLACER
ለMCPS ተማሪዎች በነፃ መሰጠቱ ይቀጥላል። የትኛውን ፈተና ስለመውሰድ ልጅዎ ከአማካሪው/ዋ ጋር መስራት አለበ(ባ)ት።
በተጨማሪ፣ የልጅዎ አማካሪ ስለ SAT ወይም ACT ዋጋ ማስወገጃ ስርአት ማግኛ አመራር ሊሰጥ ይችላል።
CCRCCA ለኮሌጅና ለስራ ዝግጁነት መጠቆሚያነት ከነዚህ ፈተናዎች በእንግሊዘኛና በሂሳብ ክፍሎች በተውሰነ ደረጃ
ውጤት እንዲያገኙ ይጠይቃል። ከነዚህ ደረጃዎች ያነሰ ውጤት የሚያገኙ ተማሪዎች ከ11ኛ ክፍል በኃላ በት/ቤቱ የተራዘመ
የትምህርት እድሎች ይሰጣቸውና ለኮሌጅና ለስራ ዝግጁነታቸውን ለማሳየት እድል ይሰጣቸዋል። ግባችን እያንዳንዱ ተመራቂ
በድህረ-2ኛ-ደረጃ ያለምንም የመገገምያ ትምህርት ለስኬት ዝግጁ ሆኖ MCPSን እንዲለቅ ነው። በዚህ ፎል መጠረሻ አካባቢ፣
ስለ ተፈላጊ ለኮሌጅና ለስራ ዝግጁነት የግምገማ ውጤቶች እንዲሁም በማጨረሻ አመታቸው ለተማሪዎች ስለሚሰጥ የተራዘሙ
የትምህርት እድሎች መረጃዎች እናጋራለን። እንደተገኘ ተጨማሪ መረጃ በMCPS ድርጣብያ ይገኛል። እባካችሁ
www.montgomeryschoolsmd.orgን ጎብኙና CCRCCAን ፈልጉ።
ጥያቄዎች ካሏችሁ፣ እባካችሁ የልጃችሁን አማካሪ ወይም የት/ቤት አስተዳደር ቡድንን አንጋግሩ።
ከምክበር ሰላምታ ጋር፣
Larry A. Bowers
Interim Superintendent of Schools
ላሪ ባወርስ
ተጠባባቂ የበላይ ተቆጣጣሪ