MONTGOMERY COUNTY PUBLIC SCHOOLS የቅድመ-መዋለ ህጻናት/ሄድ ስታርት ፕሮግራሞች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ልጆች ጨምሮ ሴፕተምበር 1 ቀን፣ 2016 እድሚያቸው 4 አመት የሚሆናቸው ልጆች ያሏቸው የገቢያቸው መጠን ለሚፈቅድላቸው ቤተሰቦች። ያለቀጠሮ ማመልከቻዎች ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ9፡00a.m.–4:00 p.m.፣ በRocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 143, Rockville, Maryland 20852 እንቀበላለን። ለመረጃ፣ በ301-230-0676 ይደውሉ። የሚከተሉትን ሰነዶች ማምጣት አለብዎት:1) የዩ.ኤስ. የልደት ምስክር ወረቀት (የዩ. ኤስ. ፓስፖርትም ተቀባይነት አለው) የዩ.ኤስ ዜጋዎች ያልሆኑ ልጆች መጀመሪያ በት/ቤት ካውንስሊንግ፣ የመኖሪያ እና አለምአቀፍ ቅበላ ጽ/ቤት (Counseling, Residency and International Admissions Office) መመዝገብ አለባቸው። ቀጠሮ ለመያዝ በለልክ ቁጥር 301-230-0686 ይደውሉ። 2) የቤተሰብ ገቢ ማረጋገጫ (በቤተሰቡ ውስጥ የሚሠሩ ወይም ገቢ የሚያገኙትን ሁሉ ያካቱ) የ2015 1040 ታክስ የተከፈለበት መግለጫ፣ እንዲሁም ሁሉንም የW2 ቅጾች፣ እና 3 ለያንዳንዱ የስራ ቦታ የቼክ ክፍያ ማስረጃ፣ የራስዎን ስራ የሚሰሩ ከሆኑ የSchedule “C” (የቢዝነሱ ትርፍ እና ኪሣራ) እና ቅጽ 1099 ያቅርቡ፤ ተጨማሪ የገቢ ምንጮች ማረጋገጫ (ይኸውም፣ የገንዘብ መጠኑን የሚያሳይ የህፃን ማሳደጊያ ድጋፍ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ወይም ህጋዊ ማረጋገጫ፣ ስራ-አጥነት፣ Temporary Cash Assistance (ጊዜያዊ የገንዘብ ዕርዳታ)፣ የቤት ኪራይ ገቢ፣ ሶሺያል ሰክዩሪቲ፣ ሕጋዊ ማረጋገጫ ያለው (ኖቶራይዝድ የሆነ) መጠኑን የሚያሳይ የገንዘብ ዕርዳታ ደብዳቤ፣ ወ.ዘ.ተ.) 3) ተቀባይነት ያለው የMontgomery County ነዋሪነት ማረጋገጫ የአሁን የንብረት ታክስ ሂሳብ (የቤት ባለቤት ከሆኑ) የሊዝ እና የአሁን የመብራት፣ የውሃ/ጋዝ ሂሳብ ተከራይ ከሆኑ እና የHousing Opportunities Commission (HOC) ደብዳቤ፣ አግባብነት ካለው የጋራ መኖሪያ ህጋዊ መግለጫ፡- የMCPS ቅጽ 335-74 (ቤት የሚጋሩ እና/ወይም ከሌሎች ጋር የሚኖሩ ከሆነ)፤ እና የቤት ባለቤት የንብረት ታክስ ሂሳብ ወይም የተከራይ ሊዝ እና የአሁን የመብራት፣ የውሃ/ጋዝ ሂሳብ፤ እና በጋራ መኖሪያ አድራሻ የተላኩ ለወላጅ/አሳዳጊ በፖስታ የተላኩ ሶስት ሰነዶች 4) የወላጅ አሳዳጊ ፎቶ ያለው መታወቂያ እና የሚመለከተው ከሆነ፣ የሞግዚትነት የፍርድ ቤት ሰነድ። 5) ተጨማሪ የሚያግዙ ሰነዶች፡-የልጅ ጥበቃ አገልግሎት ሰጭ ስም፣ አድራሻ፣ እና የስልክ ቁጥር፣ የልጅ የሜዲካል ኢንሹራንስ መረጃ፣ የተጨማሪ ምግብ ፕሮግራም ደብዳቤ፤ የሴቶች፣ የህጻናት፣ እና የልጆች (WIC) የተመጣጠነ የምግብ ፕሮግራም ሰነድ፤ የልጅ ጥበቃ አገልግሎት ድጎማ ፕሮግራም፤ የኪራይ/የመብራት፣ ውሃ/ጋዝ ድጋፍ፣ ለግል የተነደፈ የትምህርት ፕሮግራም(IEP)፤ የአሳዳጊነት/የህጻን ማሳደጊያ/ጥበቃ መስጫ ማረጋገጫ፣ አግባብነት ካለው። ት/ቤት መጀመሪያ ላይ ምደባ ለማግኘት ቤተሰቦች እስከ ኦገስት 1 እንዲመዘገቡ አጥብቀን እናበረታታለን።
© Copyright 2026 Paperzz